January 18, 2025

STATEMENT OF FAITH

የእምነት መግለጫ

አንጾኪያ የኢትዮጵያውያን ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን

የእምነት መግለጫ

አንቀጽ 1 – የእምነት አንቀጽ
ክፍል 1 – መግቢያ

የአንጾኪያ ኢትዮጵያውያን ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መሰረተ ትምህርቷ መጽሐፍ ቅዱስን ዋነኛ
አማራጭ የሌለው መሰረት አድርጋ ነው። የቤተክርስቲያኒቱ እምነት አንቀጽ አጉልቶ የሚያሳየው ብቸኛ
የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ዶግማና ቀኖና ሲሆን የሽማግሌዎች ጉባኤና ምእመኑ በዚህ ላይ የተመሰረተ
ትምህርት ይቀበላሉ።
እንደ አንጾኪያ የኢትዮጵያውያን ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አባል የእምነት አንቀጹ እውነተኛውን
የእግዚአብሔርን ቃል የሚያንጸባርቅና የሚያጸና መሆኑ ጽኑ እምነታችን ነው፡፡

ክፍል 2 – የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች

በእኛ እምነት ሰላሳ ዘጠኝ ብሉይ ኪዳንና ሃያ ሰባት አዲስ ኪዳን መጽሐፎች በመለኮታዊ ስልጣን የተጻፈ ራዕይ
ለሰው ልጆች አጎናጽፏል (2ኛ ጢሞ 3፡16-17፤ 1ተሰሎ2፡13) ። በእግዚአብሔር ሰዎች መካከል ስላለው
ግንኙነት በዚህ መጽሐፍት ጸሐፊዎች በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ዋና ቅጂውን የልቡን ሃሳብ በመግለጽ ተጽፏል።
ይህም ያለ አንዳች ተቃውሞና ሥህተት ተመዝግቧል (ዮሐ17፡17) ። ቃሎቹም የላቀውንና ብቸኛውን
ሥልጣን የሚገልጹ ናቸው(መዝ19፡7-11፤መዝ119፤ ሮሜ 10፤ 17 ዕብ 4፡12)።

ክፍል 3 – እግዚአብሔር

በመሰረተ እምነታችን እግዚአብሔር አንድ ነው (ዘዳ6፡4 ፤ 1ኛጢሞ2፡5) ይህም በሦስት ማንነት ሲገለጥ፤
እግዚአብሔር አባት፤ እግዚአብሔር ወልድ እና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው (ማቴ 28፡19፤ዮሐ
6፡27፤ዮሐ 10፡30 ፤1ኛቆሮ 3፡16)። በእሱነት በባህሪና በክብር ሶስትም አንድም ነው(2ቆሮ
13፡14)፤ዝንተ ዓለም ባህሪ (ሚል 3፡6፤ የሐዋ17፡24)፣ ህያው (ዕብ1፡8)፣
የማይለወጥ(ያዕቆ1፡17)፣ አንፃራዊ ባልሆነ በፍፁምነት ጠቢብ(ሮሜ11፡33)፣ የማይመዘን አቅም
(ኢሳ 40)፣ በእውቀቱ ፍጹም (መዝ 147፡5)፣ ፍጹም ቅዱስ (ኢሳ 6፤3)፣ ፍጹም ትክክል(መዝ
9፡16)፣ ፍጹም አፍቃሪ(1ዮሐ 4፡7-21)፣ ፍጹም ቸር(ሮሜ 3፡23-24፤ ገላ 3፡18)፣ ፍጹም
መልካም(መዝ 100፡5) እና ፍጹም እውነተኛ(ኢሳ 45፡19) በሁሉም ቦታ የሚገኝ የራሱ ተፈጣሪ
ያልሆነ ነው(መዝ 139፡7- 12)።
ክፍል 3 ሀ) እግዚአብሔር አባት
እግዚአብሔር አባት፥ በእኛ እምነት እግዚአብሔር አባት አምላክ ነው(ኢሳ 64፡8)። እርሱ ቀድሞ
እንደወሰነው ዓላማውና ፀጋው የነገሮች ጀማሪና ፈጻሚ ነው(መዝ 90፡2)፣ እርሱ ፈጣሪ ነው(ራዕ 4፡11)፣
እርሱ ምልዓተ ዓለሙን ያጸና ነው(መዝ104)፣ እንዲሁም የአማኞች መንፈሳዊ አባት ነው(1ዮሃ
5፡11)። እርሱም ከመረጣቸው ጋር ባለው ግንኙነት እራሱን በመግለጽ ይታወቃል (በዘላለም ቃል ኪዳኑ
የመረጣቸውን ከራሱ ጋር አንድ አደረጋቸው(ዘፍ 9፡9፣ 17፡7-9፣2ተኛ ሳሙ 7፡8-16፣ ኤር 31፡31-
34፣ ሮሜ 8፡29-30፣ ዕብ 10፡16) ፍጹም አፍቃሪ ነው (ኤፌ 2፡3-5)፣ ቻይ፣ በንስሃ እንዲመለሱ
እንጂ ማንም ሰው እንዲጠፋ አይወድም(ዮሓ፡3፡17፣ 1ጢሞ 2፡4፣2ጴጥ 3፡ 9)
ክፍል 3 ለ) እግዚአብሔር ወልድ
እግዚአብሔር ወልድ፡ በመሰረተ እምነታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው (ዮሓ 10፡30፣ቆላ
1፡17፣ቲቶ 3 4-5) እርሱ ፍጹም አምላክ ነው (ዮሓ 1፡1-2፣ 14፣ ዮሓ 17፡
1-5) እንዲሁም ፍጹም ሰው ነው(ፊሊ 2፡5-8)፣ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ ተጸንሶ ከድንግል ማርያም
ተወለደ(ኢሳ 7፡14፣ማቴ 1፡18-25)፣ በፍጹምነት ያለ ሃጥያት ኖረ(2ኛ ቆሮ 5፡21፣ ዕብ
4፡15)፣ ተዓምራትን አደረገ(ማቴ 11፡4-5፣ዮሓ 2፡11)፣በቂ መስዋእትን ለሃጥያታችን በመክፈል ሞቶ
ተቀበረ(ማቴ 20፡28፣ ዮሓ 1፡29፣ ሮሜ 3፡25፣ 1ኛ ቆሮ 15፡4፣ ዕብ 10፡5-14፣ 1ኛ ጴጥ 3፡18)፣
ከሞትም ተነሳ (ማቴ 28፡5-10)፣ ለሓዋርያትና ለሌሎችም ምስክሮች ተገለጠ(1ኛቆሮ 15፡5-8)፣
አረገ(ሐዋ 1፡9)፣ ከበረ(1ጢሞ 3፡16፣ ዕብ 2፡9)፣አሁንም ለአማኞች ይማልዳል(ሮሜ 8፡34)
ክፍል 3 ሐ) እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡ በመሰረተ እምነታችን መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው(ሓዋ 5፡3-4)።
እርሱም ስለሃጥያት ይወቅሳል(ዮሃ 16፡8-11) እንዲሁም በዓለም ውስጥ የሃጥያትን መዛመት ያግዳል(ዘፍ
6፡3፣ 2ኛተስ 2፡7)፣ የሰዎችን አእምሮ እና ልብ ያዘጋጃል(ሮሜ 8፡16፣1ኛ ቆሮ 2፡2-14) ከሃጥያት
ይመለሱ ዘንድ(2ኛ ቆሮ 3፡2-3፣ ሮሜ 8፡1-14) በልጁም አምነው(1ኛ ተስ 1፡2-5) እንደገና ይወለዱ
ዘንድ(ዮሃ 3፡3-7)፡፡
ማንኛውም አማኝ በንስሃ ደህንነቱን ባገኘበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ለዘለዓለም ይኖራል
(ዮሃ14፡16፣ ሮሜ8፡9፣ 1ኛቆሮ12፡13፣ ኤፌ1፡13-14፣4፡30) ። አማኞችን በሃይሉ ያስታጥቃል(ሓዋ
1፡8፣ኤፌ 3፡16)፣ እግዚአብሔርን በመታዘዝ እንደፈቃዱ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል(ገላ5፡16-
26)፣ያስተምራቸዋል(1ኛ ቆሮ2፡13-15፣ 1ኛዮሓ2፡27)፣ በቤተክርስትያን እንዲያገለግሉ ለእያንዳንዱ
እንደወደደ ስጦታዎችን ይሰጣል(1ኛ ቆሮ12፡7፣11፣ሮሜ12፡4-8፣ 1ኛጴጥ 4፡10፣ኤፌ 4፡11)።መንፈስ
ቅዱስ ስጦታዎችን አንደ የአስፈላጊነቱ ለእያንዳንዱ በማከፋፈል የክርስቶስን አካል እንዲያገለግሉና ወንጌልን
ለዓለም ሁሉ ለማዳረስ ነው(1ኛ ቆሮ 12፡4-7፣1ጴጥ4፡10)። የመንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ስጦታዎች
በተገቢውና ስርዓት በአለው መንገድ ነፍሳትን ተጠቃሚ ማድረግ ነው(1ኛቆሮ 14፡40)። ክንዋኔውም
በፍፁም ፍቅር(1ኛቆሮ14፡ 1)እንዲሁም ያለአንዳች መለያየትን በማያስከትል ሁኔታ ነው(1ኛ ቆሮ
12፡25)፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ለአንድ አማኝ በመንፈሳዊ መንገድ ብስለቱን የሚያመለክት አለመሆኑን
በማወቅ እራስን መታያና መወደሻ ጨርሶ መሆን አይገባውም(1ኛቆሮ 12፡ 11-12)።

ክፍል 4 – ቤተክርስትያን

በኛ ፍጹም እምነት ቤተክርስትያን ክርስቶስ የመሰረታት መሆኗና ራስዋም መሪዋም እራሱ ነው(ማቴ
16፡18፣ኤፌ 1፡22-23፣ቆላስ 1፡18)፣ ቤተክርስትያን ከጴንጤቆስጤ ቀን አስከ ኢየሱስ ምፅዓት
የአሉትን አማኞች ትይዛለች፡፡(ሐዋ 2፣1ተስሎ 4፡13-18፣ 1ቆሮ 15፡51-58)በመንፈስ ቅዱስ
ሃይልና ምሪት እርዳታም ቤተክርስትያን ድንቅ የክርስቶስ የማዳን ስራን ወደ ዓለም ታደርሳለች(ዮሃ
15፡26፣ሓዋ 1፡8)። የቤተክርስትያን ተልእኮዋ እግዚአብሄርን ማምለክ ማመስገን እና ማክበር ሲሆን
እንዲሁም የክርስቶስን ድንቅ የማዳን ስራ ወንጌል ወደ ዓለም ማድረስ(ማቴ 28፡18- 20፣ሓዋ 1፡8)
ቃሉንም በማስተማር(ቆላ 1፡24-28፣1ኛ ጢሞ4፡11)በጸሎት እና በምልጃ እርሱን ክርስቶስን
በመፈለግ(ሐዋ 2፡42) ቅዱሳንን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ህብረት በማድረግ እንዲራመዱ፣ እንዲያገለግሉና
በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ህብረት እንዲያደርጉና (ሓዋ 2፡42-46፣ኤፌ 4፡11-16፣1ኛ ቆሮ 14፡26) ጌታ
ለቤተ ክርስትያን የሰጣትን ስርዓት እንዲጠብቁ ነው(1ኛ ቆሮ 11፡24፣25፣ ማቴ 28፡19)፡፡ በእምነታችን
ጌታ ለቤተክርስትያን የሰጣት ስርዓት ሁለት ናቸው። እነርሱም ጥምቀት እና የጌታ እራት ናቸው፡፡

  1. ጥምቀት ለአማኞች ሲሆን ግልፅ የእምነት ምስክርነትና ለጌታ ክርስቶስ ትእዛዝ ታማኝ መሆናቸውን
    ማረጋገጫ ስርዓት ነው፡(ማቴ 28፡19)። የጥምቀት ስርዓት አማኞች የጌታን ሞት፡ መቀበሩን እና
    ትንሳኤውን የሚመሰክሩበት ስርዓት ነው፡፡ (ቆላስ 2፡12) ይህም በብቸኝነት በውሃ ውስጥ በመጥለቅ
    ይገለፃል፡፡ (ሐዋ፡ 8፡36- 39) ።
  2. የጌታ እራት ስርዓት የሚወስዱ አማኞች ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ለማሰብ እና ክንዋኔውንም
    ከመውሰድ በፊት እራስን መርምሮ በተገቢው ሰዓት መውሰድ ይገባል።(ማቴ 28፡18-20 እና 1ኛ ቆሮ
    11፡23-28)
    በእኛ እምነት ቤተክርስትያን በአጥቢያው በሚኖሩ የክርስትያኖች ሕብረት የምትመሰረትና መሪዋም ክርስቶስ
    ሲሆን ትምህርትዋም ሙሉ ስልጣን በአለው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው።(ገላት 1፡2፣1ኛ ቆሮ 1፡2፣1ኛ ተስ
    1፡1፣ራእይ 1፡11) እያንዳንድዋም አጥቢያ ቤተክርስትያን በሽማግሌዎች ጉባኤ ትመራለች፣
    ትተዳደራለችም፡፡(1ኛ ጢሞ 3፡1-7) እያንዳንዱ የሽማግሌዎች ጉባኤ አባላት በመጸሐፍ ቅዱስ
    መመዘኛ ተፈትሸው ብቃታቸው ከተመዘነ በሁዋላ ቤተክርስትያኒቱን ለመጠበቅና የምትመራበትን
    የእምነት ዓንቀጾች ያለአማራጭ አስፈጻሚ ሊሆኑ ሲችሉ ነው።(ቲቶ 1፡9) መንጋውንም ይጠብቃሉ(1ኛ ጴጥ
    5፡1-30)የቤተክርስትያንዋንም ማንኛውንም ነገር በበላይነት ይቆጣጠራሉ(ሓዋ 20፡28፣ ዕብ 13፡17)።
    ዲያቆናት ሽማግሌዎችን የቤተክርስትያንዋን ተልእኮን ለማስፈጸም በሚያደርጉት ስራ ይረዳሉ(ሓዋ
    6፡1-6፣ፊሊጵ 1፡1፣1ኛጢሞ 3፡8-13)።
    ክፍል 5 ሰው

በእኛ እምነት ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው፡፡ሰውንም ነፃ የፈቃድ ምርጫ እንዲኖረው
አድርጎ ፈጠረው፡፡ በዚህ ነፃ ምርጫው ሰው በስይጣን ተፈትኖ በመውደቅ ሃጥያትንና ሞትን ወደ እዚህ ዓለም
አመጣ። ሰውም እግዚአብሄር ያሰበለትን መልካም ሃሳብ እና ክብር ማስመለስ የሚችለው በአንድ ብቸኛ
መንገድ ሲሆን እርሱም በጌታ ሞትና ትንሳኤ አምኖ በፀጋው በመዳን ብቻ ነው።(ዘፍ1፡26-30፣
2፡7፣3፡1-24፡ መዝ 8፡4-6፣ ዕብ 2፡6-8፣ ሮሜ 3፡23-24፣ ኤፌ 2፡1-22፣ ቆላ 1፡21-22)

ክፍል 6 – የመጨረሻው ዘመን

በእኛ እምነት ጌታ ኢየሱስ በክብር ወደ እዚህ ዓለም እንደሚመጣና ቤተክርስትያንን ወደ እርሱ ለዘልዓለም
እንደሚነጥቃት ነው፡(ዮሃ 14፡2-3፣ 1ኛተስ 4፡16-17)። መጽሐፍ ቅዱስ በአፅንኦት የሚያስገነዝበን
ምጽኣቱ ባልተጠበቀ ወቅት ስለሚሆን ተዘጋጅተን እንድንጠብቅ ነው። (1ኛተስ 5፡4-6፣ ራዕ 22፡20) ።
በዚያን ጊዜ የሞቱትም በህይወት ያሉትም በቅፅበት ተለውጠው ዘልዓለማዊ የማይሞተውን አካል
እንደሚለብሱ ነው፡፡ (1ኛ ቆሮ 5፡51-53)
እግዚአብሔር በራሱ ጊዜ በራሱ መንገድ የዓለምን ፍፃሜ ያመጣል። በገባው ተስፋ ቃል መሰረት ጌታ
ኢየሱስ በታላቅ ክብር እየታየ ይመለሳል፣ ሙታን ይነሳሉ፣ ክርስቶስም በሰዎች ሁሉ ላይ በፅድቅ ይፈርዳል።
ሃጥያተኞች በፍርድ ወደ ሲኦል ለዘለዓለም ቅጣት ይወሰዳሉ፡፡ ቅዱሳን በትንሳኤ ሰውነታቸው የሚገባቸውን
ሽልማት በመቀበል ለዘለአለም ከጌታቸው ጋር በገነት ይኖራሉ፡፡ (ሐዋ 1፡11፣ቲቶ 2፡13፣ ኢሳ
2፡4፣ 1ተስ 4፡14-18፣ማቴ 24፡29-30፣ ራዕ 22፡12፣1ኛቆሮ 4፡5፣ ማቴ 25፡34፣ ራዕ 20፡15)

ክፍል 7 – መላእክት

በእኛ እምነት መላእክት መንፈሳዊ ፍጥረቶች ሲሆኑ እግዚአብሄርን እንዲያገለግሉና ከፍ እንዲያደርጉት
የተፈጠሩ ናቸው።መላእክትም የእግዚአብሄር መልእክተኞችና ሰውንም የሚያገለግሉ ናቸው። እንዲሁም
ሃያላን ሲሆኑ ፈፅሞ መለኮተ አምልኮን የማይቀበሉ ናቸው(ቆላ 1፡16፣2፡18፣ መዝ 103፡20 ዕብ
1፡13-14 ራዕ 22፡8-9)። ሰይጣን ከፍተኛ የስልጣን ተዋረድ የነበረውና በአመፃው በራሱ እና በተከታዮቹ
ላይ ፍርድን ያመጣ ነው። (ኢሳ 14፡12-15፣ሕዝ 28፡12-19፣ ዮሐ 16፡11፣ 2ኛጴጥ ፡4) ።
ሰይጣን አዳምንና ሔዋንን በእግዚአብሄር ላይ እንዲያምጹ የፈተናቸው ነበር(ዘፍ 3፡1-9፣ 2ኛቆሮ11፡3፣)
ዛሬም ከሌሎች አብረውት ከተጣሉት የወደቁ መላእክት ጋር በመሆን ሰዎችን በማታለል እና በመፈተን
የእግዚአብሄርን ሃሳብ ተቃውሞ ስራውን አንደቀጠለ ነው( 2ኛቆሮ 11፡14፣ ኤፌ 6፡10-18፣
1ኛጢሞ4፡1፣ ራዕ12፡9)።በጌታ አየሱስ የመስቀል ላይ መስዋእትነት ሰይጣን እና እርኩሳን መላእክቱ ድል
ተነስተዋል፣ በመጨረሻው የፍርድ እለት ወደ እሳት ባህር ለዘለዓለም እንዲጣሉ ተወስኖባቸዋል፡፡(ማቴ
25፡41፣ዮሐ 12፡31-32፣ 1ዮሐ 3፡8፣ ራዕ20፡10)

ክፍል 8 – የምልአተ ዓለም በውስጡም ያሉት ቀደምት ግኝት

በኛ እምነት እግዚአብሔር ፍጥረተ ዓለማቱን እና ምድርን እንዲሁም በውስጡ ያሉትን በራሱ ፈቃድ
በስድስት ቀን ፈጥርዋል። እግዚአብሔር በቀጥታ አንደየአይነታቸው እፅዋትንና እንስሳትን በመፍጠር እንደየ
ዝርያቸው እንዲዋለዱና እንዲበዙ ምድርንም እንዲሞሉዋት አዝዞዋል። የመጀመርያዎቹ ሃጥያት የሌለባቸው
ፍጹም እና ንጹህ መልካምም ነበሩ። ሰው ልዩ ነው፣ በእግዚአብሔር መልክ ከሌሎች በልዩነት ተፈጠረ።
ከሌላም ያልተገኘ ሰው ሆኖ ከሌላ ፍጡር ሳይዋረድ የተፈጠረ ሰው ነው። (ዘፍ 1 አና ዘፍ 2፣ 5፡1-
2፣9፡6፣ዘፀ 20፡11፣መዝ 33፡6-9፣ ዮሐ 1፡3፡ ቆላ 1፡16-17)
ክፍል 9 – ሐጥያት

እኛ እንደምናምነው እግዚአብሔር አዳምንና ሄዋንን የመጀመርያው የሰው ፍጡር ሃጥያት ያልነበረባቸው
ከአምላክ ጋር በፍፁም ህብረት አድርጎ ፈጠራቸው (ዘፍ 1፡26- 28፣ 31፣2፡18-24፣ ያዕ 3፡9)።
በምርጫቸው በመተላለፍ ሃጥያትን ሰሩ፣ የእግዚአብሔር ክብርም ጎደላቸው፣ተፈረደባቸውም። ሃጥያትም
ከእግዚአብሔር ለያቸው፣መከራም መጣባቸው እንዲሁም ሞት ተከተለ።
ይህም የዘር ውርስ ሆኖ ከዚያም በሁዋላ ለመጡትም ተረፈ (ዘፍ 3፣ መዝ 14፡1-3፣ 51፡5፣ሮሜ
8፡20-22) ።
የሰው ዘር ያልታቀበ ውድቀት ለበለጠ ፍርድ ብሎም ዓለም አቀፍ በጎርፍ መጥለቅለቅና ለመጥፋት ተሰጠ።
ከውሃ ጥፋት በሁዋላ የቀጠለው የሰው ዘር አመፃ በባቢሎን የእግዚአብሔርን ቅጣት በማስከተል የሰው ልጅ
ቁኣንቁዋው ተደበላለቀ፣ በምድርም ገፅ ላይ ተበተነ። (ዘፍ 11፡1-9፣ ሉቃ1፡51)
እኛም የኣባታችን የአዳምን ህጥያት ተፈጥሮ ወረሰን (መዝ 51፡5፣ ሮሜ5፡12) በመንፈሳችን ሙታን ሆነን
ተገኝን (ኤፌ 2፡1፣) በተፈጥሮአችንም ሃጥያተኞች ሆነን ተገኘን(ሮሜ 3፡10፣23፣5፡12) ውጤቱም እኛ
በራሳችን ከእግዚአብሔር አምላክ ጋር መታረቅ አልቻልንም።(ገላ 3፡22፣ኤፌ 2፡8-9፣ ሮሜ 8፡8)።

ክፍል 10 – ድነት

በኛ እምነት ከሃጥያት ድነትና ከዘለዓለም ፍርድ ቅጣት ያመለጥነው በእግዚአብሔር ፍፁም ስጦታ ነው (ሮሜ
6፡23) ። ይሀም በእምነትና በጌታ ኢየሱስ በመታመን ብቻ እንጂ አንዳችም የራሳችን የሆነ ሰብአዊ አስተዋፆ
የለበትም። (ዮሐ 3፡16፣ ኤፌ 2፡8-9፣ ቲቶ 3፡5 7)
የክርስቶስ ሞት ሙሉ እና ፍጹም ንጹህ የሃጥያት ዋጋ ሆንዋል(1ኛቆሮ 15፡3፣ ዕብ 9፡11- 15፣ 1ኛጴጥ
1፡18-21)። ይህውም የእግዚአብሔርን ፍፁም ዳኝነት ሚዛን ያሙዋላ ነው(ሮሜ 3፡23-26፣ ዕብ
10፡1-10)። በእግዚአብሔር በህይወት ለመኖር ቻልን(1ቆሮ 15፡22፣ ኤፌ2፡4-7፣ ጴጥ 3፡18)፣
ከእንግዲህ ለሃጥያት ባርያዎች አይደለንም(ሮሜ6)።የ እግዚአብሔር ልጆችም ተባልን (ዮሐ 1፡12፣
ሮሜ8፡14-17፣ ገላ 3፡26)፣የተለዩ ደቀመዛሙርት፣ በመንፈስም እንደ ልጆች የሚያድጉ ፣ ስራ ወይም
የፅድቅ አፍቃሪዎች አደረገን(ኤፌ2፡10፣ ቆላ1፡10-14፣3፡12-17፣ ዕብ12፡1-2፣ 1ኛጴጥ2፡2)።
እኛም ከማንኛውም ሃጥያት ምህረትን ተቀበልን(ኤፌ 1፡7፣ 1ኛዮሐ 1፡9) እንዲሁም በዘለዓለም እረፍቱን
በማጽናት አስገባን።(ዮሐ5፡24፣6፡39-40፣10፡27-30፣ 1ኛጴጥ1፡3-5፣ 1ኛዮሐ 5፡9-13)

ክፍል 11 – ቤተሰብ

እግዚአብሔር ቤተሰብን በመፍጠርና በመመስረት የህብረተሰብ መሰረት
አድርጉዋል። ጋብቻ የአንድ ወንድ እና የአንዲት ሴት ሙሉ ዘመን አንድነት እና ቃል ኪዳን ነው (ዘፍ
2፡23-24፣ ማቴ 19፡4-6)። ጋብቻ የሁለቱን አንድነት ህብረት ያጸናል (ዘፍ 2፡25፣ ኤፌ5፡31-33) ።
በቀደምትነት የተመሰረተው ቤተሰብ የክርስቶስንና የቤትክርስትያንን አንድነት ለመመሰል ነው(ዘፍ1፡28፣
ምሳሌ 5፡15-19፣ 1ኛቆሮ 7፡1- 5)። ክርስቶስ ቤተክርስትያንን እንዳፈቀራት ባልም ሚስቱን ያፈቅራት
ዘንድ ታዝዝዋል።ቤተክርስትያን ለክርስቶስ አንደምትገዛ ሚስትም ራስዋን ለባልዋ ታስገዛ(ኤፌ 5፡22-
23)።
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ሲሆኑ ከመጀመርያው ቀን ፅንስ ጀምሮ ሰው ናቸው (መዝ
127፡3፣139፡13-16)። ወላጆች ልጆቻቸውን የፅድቅ እሴት ምሳሌ በመሆን ማሰልጠን፣የእግዚአብሔር
ቃል ማስተማር፣ በፍቅርና በመገሰፅ መምራት፣ የጥበብ ምንጭ የሆነውን ስጦታ በመስጠትና በመምከር
ማሳደግ ናቸው(ዘዳ6፡4-7፣ ምሳ1፡8-9፣ 13፡24፣22፡6)።ወላጆች ለልጆቻቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ
በማድረግ የሚገባቸውን ማሙዋላት(2ኛቆሮ 12፡14፣ኤፌ 6፡4)ልጆች ደግሞ ወላጆቻቸውን ማክበር ፣
መታዘዝ እንዲሁም በጥገኝነታቸውና በእድሜ በደከሙ ጊዜ መጦርና መንከባከብ ሃላፊነታቸው ይሆናል (ዘፀ
20፡12፣ ዘሌ 19፡32፣ ምሳ 23፡22ኤፌ 6፡1-3፣ ቆላ 3፡20፣ 1ኛጢሞ 5፡8)።

አንቀፅ 2 – የቤተክርስትያን የህብረት ቃል ኪዳን

በክርስቶስ ውድና ክቡር ደም ለእግዚአብሔር እንደተዋጀን ሰዎች የልብ መሻታችን በክርስቶስ ሆነን አንደልቡ
መሻት በመኖር ትእዛዙን በማክበር ለቃሉ ታማኝ ሆነን “እንደጸጋው መጠን ወደ ሙላቱ ችሎት ለማደግና
የመድሃኒታችንን የጌታችን እውቀት ይበዛልን ዘንድ ነው”(2ኛ ጴጥ3፡18) እንዲሁም በእግዚአብሔር
መንፈስ ምሪት በመመራት በጸጋው ባለፀግነት የበቃን በመሆን በበዛልን የኃይሉ ችሎት መጠን በህይወታችን
የሆነውን የእርሱን ታላቅ ስራ በፍሬአችን እንመሰክራለን(ገላ 5፡16፣22- 23)። ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ
(66 መጽሐፍት) በመቀበልና ቃሉንም የእምነት መሰረት በማድረግ ትምህርቱን ያለግድፈት ሁሉን
በሚያስችለን የጸጋው ባለጠግነት መጠን በመቀበል ለመኖር እንፈልጋልን። የሚከተሉት ግልጽና ዝርዝር
ግቦች ተስፋና ምኞታችን ናቸው፡

ክፍል 1- ለእግዚአብሔር መለየት

የኛ ፍላጎት “ከማንኛውም የስጋ ስራ መገለል” (1ኛጴጥ 2፡11) ከአለው የአለማዊነት ክፉ ምኞት
መጠበቅ (ሮሜ 12፡2) እንዲሁም “የእኛን አባላት ለበጎ ስራ የበረቱ በማድረግ ለፅድቅ በጎ እቃ አድርጎ
ለእግዚአብሔር ማቅረብ ነው (ሮሜ 6፡13)።

እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ( ታላቁ ትእዛዝ)

እኛ ዓላማችንና ምክራችን እርስ በእርስ ተፋቀሩ ነው። ”ያለ ማስመሰል ባህሪ” (ሮሜ 12፡9)፣
በአስፈላጊው ወቅት እርስ በእርስ ለመረዳዳት፣ እንዲሁም ለቅዱሳን ሁሉ
በመጸለይ (ኤፌ 6፡18) የኛ ጥረት በማንኛውም መንገድ “የመንፈስን አንድነት እየጠበቅን በሰላም
ሰንሰለት መቀናጀትን ነው” (ኤፌ4፡3) ከመራርነት፣ ከጩሀት፣ ከቁጣ እና ከክፉ ቁዋንቁዋ መቆጠብ
ነው” (ኤፌ 4፡31)

የአገልግሎት ተልእኮአችን ቃል ኪዳን

የእኛ ዓላማ ቤተክርስትያኒቱን በታማኝነት መርዳት ይሄውም በሁሉም ተልእኮዋ በአገልግሎት ስብሰባዎችዋ
በመገኘት፣ በትጋት መንፈስ ቅዱስ ለያንዳንዳችን የሰጠንን ስጦታ የሚተገብሩ ወኪሎች ሆነን ማገልገል፣
እንዲሁም ጌታ እንደተናገረ በልግስናና በፍፁም ደስታ ለጠራን አገልግሎት ዋጋ በመክፈል ማገልገል (1ኛ
ቆሮ 16፡2፣2ኛ ቆሮ 9፡4-5)

ክፍል 4 – ጥራት ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ማስተማር

እኛ ዓላማችን “በቅንነት ተወዳዳሪ በሌለው ታማኝነት ለቅዱሳን ቃሉን በማቅረብ መመገብ እና ማገልገል
ይሆናል”(ያዕ 3)። “እውነትንም በፍቅር በመናገር(ኤፌ 4፡15) በእምነት አንቀጻችን አስፈላጊ የሆኑ
ሃሳቦች ተካትተዋል፣ እነዚህንም እውነቶች ያለይሉኝታ በፅናትና በግልፅ በማስቀመጥ እናስተምራለን፣
እንዳይከለሱም እንጠብቃለን።

ክፍል 5 – ዓለምን በክርስቶስ መድረስ (ታላቁ ተልእኮ)

የኛ ዓላማ በቃልና በተግባር ለአልዳኑ ነፍሳት በመመስከር በክርስቶስ አምነው እንዲድኑና የአጥቢያ
ቤተክርስትያን ህብረት እንዲሆኑ ማድረግ ነው። በተጨማሪ በትጋት በአጥቢያ እና በውጪ የሚከናወኑትን
የወንጌል ተልእኮዎችን እንደ አቅማችን ጌታ በረዳን መጠን የምንችለውን በመርዳት ወንጌል ለሰው ሁሉ
እንዲዳረስ ማድረግ ነው(የሐዋ ስራ 1፡8)።
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መርቶኝ ጌታ ኢየሱስን አንደግል ኣዳኜና ጌታዬ
የተቀብልኩ፣ የጌታ መንፈሳዊ አካል በሆነችው በአንጾኪያ የኢትዮጵያውያን ወንጌላዊት ቤተክርስትያን
ውስጥ በህብረት ለማምለክና ህብረት ለማድረግ በመፈለግና
በቤተክርስትያኗ መንፈሳዊ ጥበቃ ውስጥ ለመከለል በመወሰን ይህን የእምነት አንቀፅ መመርያ እና
የትምህርትዋ መመርያ መሆኑን ተቀብዬአለሁ።


እኔ………………………………….
ከአንጾኪያ የኢትዮጵያውያን ወንጌላዊት ቤተክርስትያን አባላት ጋር ቃል ኪዳን
ለመግባት መወሰኔን እገልጻለሁ።
ፊርማ…………………………………..
ስም፡………………………………….ቀን………………..

ሽማግሌ………………………………ቀን………………