January 18, 2025

Vision, Mission & Values

የኢየሱስ ክርስቶስን ፈለግ በመከተል የምትኖርበትን ማሕበረሰብ ወደ እግዚአብሔር መንግስት እውነት የምትመራና የምታሳድግ ቤተ ክርስቲያንን ማየት ነው ።

ሰዎችን ወደ ወንጌል እውነት በመጋበዝ፣ በሕብረት አምልኮ፣ በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ  ለእግዚአብሔር ክብር እንዲኖሩ ማድረግ።

ፈለገ ክርስቶስ: የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት የአገልግሎታችንም ሆነ የኑሮአችን መለኪያ ነው

የመንፈስ ቅዱስ ማእከላዊነት: ክርስቶስን መስሎ ለመኖርም ሆነ ለማገልገል መንፈስ ቅዱስ ማእከላዊ እንደሆነ እናምናለን

በቃሉ መኖር: የእግዚአብሔር ቃል የሕይወታችንና የአግልግሎታችን መሰረት ነው

የጸሎት ሕይወት: ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ሕብረት የአገልግሎታችን መሰረት ነው

አንድነትና ፍቅር: የጋራ አምልኮ፣ የእምነት አንድነትና የተገለጠ ፍቅር መታወቂያችን ነው

ተልእኮአዊ: የክርስቶስን ህይወት በቃል እና በኑሮ ለሌሎች ማሳየት

ሁለንተናዊ: ክርስቶስ የማይነካው የሕይወታችን ክፍል የለም